Song Lyrics

ሌላ ነገር ይቅር

Pastor Tamrat Haile
Bedibibikosh Kenu Endayalf
ሌላ ነገር ይቅር ይወራ ስለ እርሱ በከበረው ደሙ ኃጢአት መደምሰሱ (2x) እንዳች ሳይባል ሁሉም ሰው ይመነው ኢየሱስን ማጣት ሁሉንም ማጣት ነው (2x) የባህል እስርአት የኃጢአት ቁራኛ እስከመቼ ድረስ እያለን መዳኛ ብርድና ኩነኔ ለከደነው ሁሉ መቃብርን ከፋች ኢየሱስ አለ በሉ አዝ፦ ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ ስለኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ቃሉን ስለናቅን በአዳም መተላለፍ ሁሉም ሰው ወደቀ (2x) የዓለምን ኃጢአት በእንጨት ሊሸከም ሥጋ ለብሶ መጣ ሁለተኛው አዳም (2x) ምርኮኛን የሚያስለቅቅ እስራት የሚያስፈታ ምህረትን ይዞ የመጣውን ጌታ አምኖ ይቀበለው የሰው ዘር በሙሉ ኢየሱስ ያድናል የምስራች በሉ አዝ፦ ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ ስለ ኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት ሰይጣን የአገዛዝ ቀንበሩን ሲያከብድ የዓለም እንቆቅልሽ እየበዛ ሲሄድ (2x) ኃያላን ነገሥታት ፈላስፎች ቢሆኑ ሊያድን የተቻለው ማነው ለመሆኑ (2x) የመዳንን እራስ በመስቀል ፈጽሞ ቤት ሊያዘጋጅልን የሄደልን ቀድሞ በሕያዋን በሙታን ሊፈርድ የሚመጣው የጽዮን ሙሽራ ጌታ ኢየሱስ ነው አዝ፦ ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ ስለ ኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection