አዝ፦ ክብር ለክብር ጌታ ውዳሴና ዕልልታ አምልኮና ስግደት ኢየሱስ ይሁንለት (2x) ኢየሱስ ይሁንለት (4x) በላይ በሠማይ ያሉ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ቀን የላቸው ሌሊት ሁልጊዜ የሚያከብሩት ዘለዓለማዊ ንጉሥ ኃያል የክብር ጌታ መጽሐፉን የከፈተ ማኅተሙን የፈታ አዝ፦ ክብር ለክብር ጌታ ውዳሴና ዕልልታ አምልኮና ስግደት ኢየሱስ ይሁንለት (2x) ኢየሱስ ይሁንለት (4x) የወደቁ መላዕክት አጋንንት በጥልቅ ያሉ ስሙ ሲጠራባቸው ሁሌ ይንቀጠቀጣሉ ተራሮች ሚጤሱለት ኮረብቶች ሚዘሉለት ጌታ የጌቶች ጌታ ኢየሱስ የጽዮኑ ዓለም አዝ፦ ክብር ለክብር ጌታ ውዳሴና ዕልልታ አምልኮና ስግደት ኢየሱስ ይሁንለት (2x) ኢየሱስ ይሁንለት (4x) በፍጥረት መጀመሪያ ከሙታንም በኩር ሁሉ በእርሱ የሆነ ኢየሱስ ቃለ እግዚአብሔር ፀጋ እውነትን ተሞልቶ በእኛ ዘንድ ያደረ ክርስቶስ አልፋ ኦሜጋ ያለና የነበረ አዝ፦ ክብር ለክብር ጌታ ውዳሴና ዕልልታ አምልኮና ስግደት ኢየሱስ ይሁንለት (2x) ኢየሱስ ይሁንለት (4x) ከዘር ከነገድ ሁሉ ከአገር ከወገን እኛን በደሙ አጭቶ ካህናት ያደረገን መንፈሱን ያፈሰሰ ፀጋውን የሰጠን የናዝሬቱ ኢየሱስ ክብር ለእርሱ ይሁን አዝ፦ ክብር ለክብር ጌታ ውዳሴና ዕልልታ አምልኮና ስግደት ኢየሱስ ይሁንለት (2x) ኢየሱስ ይሁንለት (4x)