ሰርግና ምላሹ ድግሱ ቀለጠ ከትላንቱ አጀብ የዛሬው በለጠ የፍቅር ጨዋታው ከመቼው አለቀ የፍቺ ጥያቄ ፍርድ ቤት ዘለቀ ጭብጨባው መልካም ነው ዕልልታም ባልከፋ አስቸገረን እንጂ አንገት እያስደፋ (2x) ትዳር ይከበር ቃልኪዳን ይጽና በመካከሉ አምላክ አለና መፋታትን እጠላለሁ ብሏልና ስብከት ሙያ ሆኖ ወንጌልም ለእንጀራ መዝሙሯ ጸሎቷም . (1) . ተቸርችራ ገበያው ቀለጠ ቤተመቅደስ ደጃፍ ጌታ ተመልሶ እስኪያነሳ ጅራፍ ምን ትጠብቃለህ ሰብስብ ኮተትህን ያሸጥሃል ኋላ በኩርነትህን (2x) ወንጌል ይሰበክ በእውነት በጽድቅ በድብብቆሽ ቀኑ እንዳያልቅ መክሊት ሰጪ አለ ጌታ ሚጠይቅ ወንድሞች ተጣሉ በመሪነት ሰበብ ያውም በመድረኩ ጉድ እን ሽማግሌም ልግዛ መጋቢው ልንገሥ በኧረኞች ትግል መንጋ ሲታመስ በብዕር በቃላት ጦፈ ክርክሩ እስቲ መልሱልኝ የማነው ወንበሩ (2x) መንጋው የኢየሱስ የሞተለት የበረቱን ቁልፍ አስረክቡት የእኛ ጥሪ ዝቅታ ነው ሎሌነት ነጭ ጥቁር ቀለም መለየት አቅቶት ድንበር የጣሰ ይላል ምናለበት ጽድቅ ከአመጽ ጋር ብርሃን ከጨለማ አምላክ ያጣላውን ማን አለህ አስማማ ይልቅ ከዓለም ተለይ ውጣ ተቀደስ የትም እየረገጥክ ቤቱን አታርክስ (2x) እልፍ በል ውጣ ተለይ ስሙ ተጠርቷል በአንተ ላይ የሚመጣ ሙሽራ አለህ ከሠማይ ሆድም ለመብል ነው መብልም ለሆድ ሁሉም ይጠፋሉ ብንወድም ባንወድ አንዳንዴም በመጾም ጐሽም ሥጋህን አብልቶ ከሚዘርፍ አስጥል ፀጋህን እንቅልፍም አይብዛ አርግለት ገደብ ጸሎት አይረሳ ቃሉም ይነበብ (2x) ተነስ ተጋደል ጸንተህ ተዋጋ ያበረታሃል የአምላክህ ፀጋ የትም መቼም ጌታ እንዳለ አትዘንጋ