Song Lyrics

ጌታቸው በመጣ ጊዜ

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Nekagn Bedinget
አዝ፦ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሮች ብጹኁን ናቸው ( 2x) አስቀምጦ ያገለግላቸዋል በማዕዱ እኔንም አርገኝ ከእነርሱ እንደ አንዱ ቀጠሮ አፍራሽ የጊዜ ሌባ መምሸቱን አውቆ ቤቱ ማይገባ ከዘመን ኋላ ኋላ ተጎታች የሁሉም ጭራ ከሁሉም በታች ከቶ የማይገባኝ የህይወት ነገር እንዳልሆንብህ እንዳትቸገር እግሬ መራመድ እንዳያቅተው የሩቁን እንዳይ አይኔን ክፈተው ዓለም ስትከፋ ዘመን ሲጨልም ምርምር በዝቶ እምነት ሲደክም ፈጣሪን መፍራት ከምድር ሲጠፋ ፍጥረት ሲደገፍ በራሱ ተስፋ ቆይ ይደረሳል ማለት ይበቃል ነገን መኖሬን እግዚአብሔር ያውቃል ይልቅ ልነሳ ልክፈተው ደጁን መለከት ልንፋ ልንገር አዋጁን የመምጫውን ቀን ከቶ ማን ያውቃል ጠብቁኝ ብሎ ያስጠነቅቃል የድል መለከት ሲነፋ ከላይ አንዷ በወፍጮ ሌላው በእርሻው ላይ ምጥ እርጉዝን ሴት እንደሚይዛት ድንገት ይሆናል የጌታ መምጣት በውጭ ጨለማ መጣል ይመጣል በተጠንቀቅ ግን መቆም ያዋጣል የማጽናኛ ቃል ለደከሙቱ የጥሪ ደወል ውጪ ላሉቱ በህይወት ማእበል ለሚንገላቱ የጸሎት ድጋፍ እንዲበረቱ አልነጋ ላለው ለጨለመበት መቆም እንድችል በፈረሰበት ባርከኝ በብዙ አታሳንሰኝ እየቆራረጥክ ለብዙ አድርሰኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection