Song Lyrics

አምንሃለሁ

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Nekagn Bedinget
ፀጋህ ለእኔ በዝቶ እዚህ ደርሻለሁ አንተ ከቆምክልኝ ሌላ ምን እሻለሁ የገፋኝ ተገፍቶ የወጋኝ ተወጋ ያልያዝኩትን ልያዝ እጆቼን ልዘርጋ ባለሁበት አልሂድ ጊዜ አይለፍብኝ እስቲ ከመንፈስህ እፍ በልብኝ አዝ፦ አምንሀለው ጌታ አምንሀለው ቃልህን ስታከብር አይቻለው አምንሀለው ጌታ አምንሀለው ከግብጽ ወጥቼ ምድረበዳ ዘለኩ ባህር ተሻግሬ ዮርዳኖስን አለፍኩ እያሪኮ በራፍ ቆሜ ለምን ላልቅስ የትላንቱን ጌታ ልታመን ይልቅስ የግብጽን ሰራዊት ባህር ያሰጠመ እግዚአብሔር ብርቱ ነው ዛሬም አልደከመም አዝ፦ አምነዋለው ጌታን አምነዋለው ቃልኪዳኑን ሲያከብር አይቻለው ( 2x) አምነዋለው ጌታን አምነዋለው የኤናቄል ልጆች ቁመናቸው ሎጋ ውስጣቸው ባዶ ነው በእምነት ልጠጋ በእነርሱ አይን ስታይ አንበጣ መስላለው በውስጤ ያለው ግን ኃያል እግዚአብሔር ነው እስከመቼ ድረስ ፈርቼ ልኑር ተሻግሬ ልውረስ የተስፋይቱን ምድር አዝ፦ አምነዋለው ጌታን አምነዋለው ቃልኪዳኑን ሲያከብር አይቻለው ( 2x) አምነዋለው ጌታን አምነዋለው እምነት ከመስማት ነው መስማትም በቃሉ ለሚመረምሩት መልስ አለው ለሁሉ ቃሉን እያነበብኩ ተስፋውን ባላምን ጊዜ ማጥፋት እንጂ መመላለስ ለምን በአባቶቼ ዘመን ድንቅን ያደረገው የጠራኝ እግዚአብሔር የጌቶች ጌታ ነው አዝ፦ አምነዋለው ጌታን አምነዋለው ቃልኪዳኑን ሲያከብር አይቻለው ( 2x) አምነዋለው ጌታን አምነዋለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection