Song Lyrics

በሞቱ እንድመስለው

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Nekagn Bedinget
አዝ፦ ወደ ሙታን ትንሳኤ ለመድረስ ቢሆንልኝ በሞቱ እንድመስለው (፱x) የእምነት አባቶቼን ሳስባቸው በደም የደመቀ ታሪካቸው በወህኒ በስራት በመከራ ፡ በጉድጓድ በዋሻ በተራራ የተቅበዘበዙ እሳት የበላቸው ለቃልኪዳን እንጂ መቼ ለእንጀራቸው ምሳሌነታቸው እንድከተል አርገኝ በልክስክስ ቦታ ከመሞት ጠብቀኝ ሰው ሁሉ ቢክድህ እኔ አልክድህ ካንተ ይልቅ እራሴን አልወድ ብዬ ስመጻደቅ ስቀናጣ ያቺ ፈታኝ ሰዐት ስትመጣ ኢየሱስን አላውቅም ብዬ እንዳልራገም አፌን ጠብቅልኝ ዛሬም ቢሆን ነገ መስቀሌን አግዘኝ ብለህ ስትለምነኝ ፡ የዓለምን እሳት ከመሞቅ አድነኝ የአንድ ሰሞን ወሬ ክብር ዝና መስቀል ያልፈተነው ጉብዝና የአንድ ሰሞን ሙቀት ሀሌሉያ አይሆንም መለኪያ መታወቂያ ካላለፍኩኝ በቀር ያቺን ቀውጢ ሰዓት አንተን አስከብሬ በመከራ እሳት ፍጻሜዬ እንዲያምር ጉዞ እንዲሰምርልኝ ጌታ ሆይ ፈሪ ነኝ እምነት ጨምርልኝ ደካማው ስጋዬ ሲስገበገብ የዓለም ነገር እንደው አይጠገብ አንዱን ስይዝ ሌላው እንዳያምረኝ ኑሮዬ በቃኝ ማለትን አስተምረኝ ስለ ስምህ ክብር ለመንግስትህ መስፋት ሁሉን መስዋአት ላድርግ ለሚጠፉ ነፍሳት ገንዘቤ ገንዘብህ ቤቴም የአንተ ቤት እንድሞት አድርገኝ የጻድቃንን ሞት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection