አዝ፦ ጌታ ሆይ ( 2x) አንድ ሰው ስጠን የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት ቢባርክ የሚደርስለት ቢረግም የሚሆንለት ቢገስፅ የምንሰማው ቢቆጣን የምንፈራው ስንተኛ የሚያነቃን ስንሮጥ የሚያቆመን ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን ( 2x) ፍቅርን ተቀብሎ የሚሰጥ የፍቅር መጋቢ ሀብታም ደሀ ብርቱ ደካማ ሁሉንም ሰብሳቢ በፍቅር በርህራሄ በትዕግስት መንጋህን ሚመራ የቆሰለ ፈዋሽ መድኃኒት ደራሽ በመከራ ጩኸት አብዝተናል ውድድር እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ሁላችንም እኩል ሆነናል የለም መደማመጥ እረፉ የሚለን ተቆጪ እንደምን እንጣ ጌታሆይ እባክህ አንድ ሰው በቅባትህ አውጣ ቃሉ ከምድር ጠብ የማይል ቀንዱ ዘይት የሞላ ለተገፉ ድሆች ተሟጋች ጉቦ የማይበላ ለእውነት ኖሮ ለእውነት የሚሞት በዚህ ክፉ ዘመን ነገስታት ሲያጠፉ ሀይ የሚል ሳሙኤልን ስጠን ቅድስት ከተማ ቅጥሯ ፈርሶ መቅደሱ ሲቃጠል በንጉስ ጮማ በወይን ጠጅ የማይቀማጠል ህዝብህን የሚያነሳሳ ቅጥሩን ለመጠገን ክብሩን ስለ ክብርህ የተወ ነህምያን ስጠን ሙሴ ወይ ኢያሱ ኤልያስ ዼጥሮስ ቢሆን ዻውሎስ ብቻ ጌታችን ሆይ አንድ ሰው አስነሳ በመንፈስ አደባባይ ሞልቶ መፍሰሱ ምን አለው ቁም ነገር አንተ የቀባኸው አንድ ሰው ይበቃል ለሀገር