ፀጋህው እንጂ ጽድቄን አልቆጥር ከሰጠኝ በላይ ምንም አልጨምር የማልጠቅም ባርያ ታሪክ የሌለኝ አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ እንዳዳነኝ አዝ፦ አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x) ማንስ ይከሰኛል አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x) ማን ይቃወመኛል ሞትና እርግማን ተጭኖኝ ነበር ነፍሴን አጉብጧት የሀጥያት ቀንበር የዓለም ብርሀን ኢየሱስ ሲመጣ ጨለማዬ ተወገደ ለእኔም ብርሀን ወጣ አድራሻ የለኝ መነሻ ስፍራ ሥሜ አይታወቅ ዘሬ አይጠራ እንዳላሰብኩት በውን በህልሜ ከነአብርሀም ከነዳዊት ተመዝግቧል ሥሜ ብርሀኔና መድኃኒቴ ነው ታዲያ እሱን አልፎ ሚነካኝ ማነው ማንስ ቢመጣ ምን ያደርገኛል የጸና ግንብ የእሳት አጥር ኢየሱስ ሆኖኛል ከተደረገው ከሆነው ነገር ጥቂቱም አይገባኝም ነበር ሞልቶ እስከሚፈስ አየሁ ምህረቱን ሁሉ ከእርሱ ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ክብር ይሁን አዝ፦ ሀሌሉ ሀሌሉያ (፬x) ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ሁሉን የሚገዛ ስራው ታላቅና ድንቅ ይገባዋል ለዘለዓለም እኛ ልናንስ እርሱ ሊልቅ በመንገዱ ጻድቅ በፍርዱ እውነተኛ ለቃሉ ታማኝ ነው ለስሙ ቀናተኛ ከትንሳኤ በኩር ከፍጥረት መጀመሪያ አልፋና ኦሜጋ መክፈቻና መዝጊያ የቤተ ክርስቲያን ራስ ያለና የሚመጣ የጌቶች ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የርስታችን መያዢያ ለቤዛም ቀን ያተመን ወደ እውነት የሚመራን በመከራም ሚያቆመን በሀይሉ የሞላ ስጦታውን ያደለን ከሰማይ የተላከ መንፈስ ቅድስ አለን እግዚአብሔር አብ ልጁን ሰጠን እግዚአብሔር ወልድ እራሱን ሰጠን መንፈስ ቅዱስ ቃሉን ሰጠን ቃሉም እኛን ለወጠ ቸር አምላክ ባለጸጋ ዘወትር እጁን የዘረጋ አያልቅበት ሁሌ ሙሉ ሀሌ ሀሌሉያ በሉ