አዝ፦ ማንን እንደጣለ ይጥልሀል ማንን እንደተወ ይተውሀል ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል ሁሉን ያደርግ ዘንድ ቻይ ነውና አምላኬ እጠብቀዋለው ፊቱ ተንበርክኬ ፡ አዋጅን በአዋጅ ሲሽር ሰምቻለው እሳትን በእሳት ሲያጠፋ አይቻለው አዝ፦ ማንን እንደጣለ ይጥልሀል ማንን እንደተወ ይተውሀል ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል የቆሸሸን ታሪክ ከማህደር ያወጣል ልብን ብቻ አይደለም ስምን ይለውጣል በሰው የተናቁ መንገድ የተጣሉ ብዙዎች ናቸው በርሱ አንቱ የተባሉ አዝ፦ ማንን እንደጣለ ይጥልሀል ማንን እንደተወ ይተውሀል ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል ለሰይጣን ሹክሹክታ ጆሮህን አትክፈት ጌታ ያነሳሀል ዛሬ ካለህበት ሁሉም ነገር አልፎ ታሪክ ታወራለህ ስለክብሩ ቆመህ ትመሰክራለህ አዝ፦ ማንን እንደጣለ ይጥልሀል ማንን እንደተወ ይተውሀል ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል እንደ አውራ ጎዳና ሆነህ መራገጫ ሁሉም ለምኞቱ አርጐህ መወጣጫ እንደወደክ አትቀር እንደተረሳህ ጨው ነው የምትሆነው ጌታ ሲያነሳህ