Song Lyrics

በቀኑ መጨረሻ

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Nekagn Bedinget
አዝ፦ ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ አንተን በመፍራት አሳድገኝ ቅጠሌን አይተው የተነሰጡ ፍሬን ፍለጋ ቤቴ ስነጡ በጣፋጭ ዜማ እየጠራሁኣቸው ያለ ዉሃ እንዳሸኛቸው ። አዝ፦ ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ አንተን በመፍራት አሳድገኝ ስምህ ተጠርተው ድንቅን ስሰራ የኔ ገድል እንዳይወራ መድረኩም እንኳ ብነቃነቅ አንተን አክብሬ ራሴን ልናቅ። አዝ፦ ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ አንተን በመፍራት አሳድገኝ የውርንጫዋ የስራ ድርሻ ወደ ኢየሩሳሌም መድረሻ ጨርቅ ብነጠፍ ሆሳዕና ብባል ክብር ስግደትም ላንተ ይገባል። አዝ፦ ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ አንተን በመፍራት አሳድገኝ ባመጽ ተወልደን በኃጢኣት አድጋናል በጎውን ነገር ማን ያሳየናል በሚለው ትውልድ መካከል ስገኝ እውነትን ገላጭ ብርሃን አድርገኝ። አዝ፦ ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ አንተን በመፍራት አሳድገኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection