Song Lyrics

እለምንሃለሁ አንድ ነገር

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Nekagn Bedinget
በሳር ብንሰራ ባገዳ ተቃጥሎብን እንዳንጎዳ የሚያነጥር እሳት ሲመጣ ማነው ተፈትኖ ሚወጣ አዝ፦ ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር የተናገርኩትን እንድኖር ( 2x) እርዳኝ በዚህ ዘመን በጨለማ የተሰወረ ፡ በማስመሰል ኑሮ የኖረ ወደ ብርሀን ታወጣለህ ለሁሉም እንደስራው ትከፍላለህ አዝ፦ ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር የተናገርኩትን እንድኖር ( 2x) እርዳኝ በዚህ ዘመን አንዳንዱ ለደሞዝ ይሰብካል ሌላኛው ለጥቅም ያመልካል ታዲያ ማነው አንተን ፈላጊ የተናገረውን አድራጊ አዝ፦ ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር የተናገርኩትን እንድኖር ( 2x) እርዳኝ በዚህ ዘመን ባፌ ብዙ ፍቅርን ስገልጥ ወንድሜን በነገር ስረግጥ ቃል አባይ ሆኜ እንዳልገኝ ጌታ ሆይ ከሀሰት ጠብቀኝ አዝ፦ ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር የተናገርኩትን እንድኖር ( 2x) እርዳኝ በዚህ ዘመን በጓዳም ይሁን በጎዳና ነውር የሌለባት ህሊና በ እግዚአብሔርና በሰው ፊት እንድራመድ እርዳኝ በእውነት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection