አዝ፦ በአዝመራ ጊዜ መኝታ በጽሞና ጊዜ ጫጫታ የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን ጊዜ እንዳያመልጠን መከራው እግሩን ከማውጣቱ አቆምን መንበርከክ በፊቱ የጸሎት መሰዊያ አፈረስን መስሎናል ሰማይ የደረስን የምድረበዳው ትውልድ በውነ በወጉ አያውቅም ጦርነት መሬትን አልረገጠም በእግሩ አታሎት እሩጫው ግርግሩ አዝ፦ በአዝመራ ጊዜ መኝታ በጽሞና ጊዜ ጫጫታ የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን ጊዜ እንዳያመልጠን እርስ በርስ እየተሟሟቅን ነፍሳትን ተዘርፈን አለቅን መርከቡ መልህቁን ዘርግቶ ይጣራል ተሳፋሪ ጠፍቶ ይቺ አለም ካልደረስንላት ጨውና ብርሀን የላት ህመሟ ሄደ እየቀጠለ መድሀኒት በእጃችን አለ አዝ፦ በአዝመራ ጊዜ መኝታ በጽሞና ጊዜ ጫጫታ የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን ጊዜ እንዳያመልጠን ተባባልን እኔ ካንተ አላንስም ታወቅን ጌታ ባልሰጠን ሥም ተራራቅን አጥር እያጠበቅን ለፍቅር ክፍያ ጠየቅን በእልህ ሳይሰፋ ገደሉ ለበደልን ላጎደልነው ሁሉ ንስሀ እንገባለን ፊትህ ጌታ ሆይ ይምጣልን ምህረትህ