አዝ፦ አለኝ ቀጠሮ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ እስኪ ልነሳ ቤቴን ላሰናዳ (2x) ሰዓቱ አይታወቅ መምጫው እንደ ሌባ ኮቴው አይሰማም ሲወጣ ሲገባ ድምፁ ሰው አይረብሽ አያውክ ጩኸቱ በድንገት ይሆናል የኢየሱስ መምጣቱ አዝ፦ አለኝ ቀጠሮ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ እስኪ ልነሳ ቤቴን ላሰናዳ (2x) እንግዳ ጋብዤ ምንድነው መኝታ ለቀን ምሳ ልስራ እራቱን ለማታ ነቅቼ ልጠብቅ የሕይወቴን ጌታ ወገቤን አጥብቄ ልበል ማራናታ አዝ፦ አለኝ ቀጠሮ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ እስኪ ልነሳ ቤቴን ላሰናዳ (2x) ላልዳኑ ልመስክር የዳኑትን ላፅና ትእዛዝ አልጠብቅም ተግባሬ ነውና ቅዱስ ቃሉን ላጥና በፀሎትም ልትጋ የገሃነምን ደጅ በስሙ ልዋጋ አዝ፦ አለኝ ቀጠሮ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ እስኪ ልነሳ ቤቴን ላሰናዳ (2x) ሕይወት መቅኖ የለው ያልፋል እንደ ጤዛ ልቦናዬን ላጥራ እስኪ እራሴን ልግዛ ስለ ኀጢአቴ አምርሬ አለቅሳለሁ ለንስሐ ፀሎት ፆም እቀድሳለሁ አዝ፦ አለኝ ቀጠሮ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ እስኪ ልነሳ ቤቴን ላሰናዳ (2x) የበደልኩትን ሰው ይቅርታ ልጠይቅ የበደለኝም ካለ ፈጥኜ ልታረቅ እርሾና እርም ይዜ መኖርም ይቅርብኝ ከፍቅር በስተቀር እዳ እንዳይኖርብኝ አዝ፦ አለኝ ቀጠሮ ኢየሱስ ከሚባል እንግዳ እስኪ ልነሳ ቤቴን ላሰናዳ (2x)