አዝ፦ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ በግብጻውያን በደል በዓመጻቸው ቁጣህ ከላይ ወርዶ ሲፈጃቸው ደምህ ተቀብቶ በመቃኔ ምክንያት ሆኖልኛል ለመዳኔ ተጠነቀክልኝ እንዳልጠፋ ዙፋንህ ከፍ ይበል ይንሰራፋ አዝ፦ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ ከኃጤአቴ በቀር ከመርከሴ የማውቀው የለኝም ስለራሴ አንተን ግን አውቃለሁ ስታድነኝ የድሃ አደግ አባት ስትሆነኝ ያረካህ እንደሆን ይኸው መልሴ ምስጋና እና ክብር ከውዳሴ አዝ፦ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ በኮሬብ ተራራ በእሳት አምሳል ለነብዩ ሙሴ ተገልፀሃል በእኔም ልብ አንድደህ የፍቅር እሳት ምስኪኑን ሕይወቴን ስታጋያት አይቻለሁ እና እንዳቅሜ አመሰግናለው ይኸው ቆሜ አዝ፦ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ አጋጣሚ አይደለም ያገናኘን እንደ አባት እና ልጅ ያቆራኘን ለእኔ ያሰብከው ያኔ ድሮ ዛሬ ተፈፀመ ዘመን ቆጥሮ በፍቅር ይዘኸኛል በውዴታ እኔም ላመስግንህ በእልልታ አዝ፦ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ