Song Lyrics

ማን ነው ያነጋው

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Genana New
አዝ፦ ማነው ያነጋው ሌሊቱን ማነው ያጠፋው እሳቱን ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ (2x) በአንድ መንገድ የመጡ በብዙ በሺህ ሲወጡ እየወደቁ ሲነሱ ክብርን ለጌታ ሲሰጡ የናቀኝ ሁሉ ሲያከብረኝ በክብር ስሜ ሲጠራኝ ዕድሜ ሰጥተኸኝ አየሁኝ የአንተ መሆኔ አኮራኝ (2x) አዝ፦ ማነው ያነጋው ሌሊቱን ማነው ያጠፋው እሳቱን ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ (2x) ከባቢሎን ወንዞች ማዶ ከምርኮ ከስር ከተማ የመውጣት ነገር ሲነገር የነፃነት ድምፅ ሲሰማ ደወል ሲመታ በድንገት ኧረ የማንልብ አመነ ምን ያቅትሃል ጌታችን አንተ ስላልከው ግን ሆነ (2x) አዝ፦ ማነው ያነጋው ሌሊቱን ማነው ያጠፋው እሳቱን ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ (2x) በባእድ ምድር እያለን የታመቀውን እሳት ጌታ ሊያነደው ጀመረ አዲስን ምእራፍ ሊከፍት ከዛፍ ወረደ ማሲንቆ ከዛፍ ወረደ በገና የፅዮን ዝማሬ ልንዘምር አዲሱን ቅኔ ምሥጋና (2x) አዝ፦ ማነው ያነጋው ሌሊቱን ማነው ያጠፋው እሳቱን ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ (2x) እያለቀስን ወጥተናል በሃዘን ዘርን ዘርተናል በምድር በሠማይ መካከል እንባችንን ረጭተናል የዜማ ጊዜ ደረሰ ነዶአችንን ይዘን መጥተናል በውዳችን ተደግፈን ከምድረ በዳ ወጥተናል (2x) አዝ፦ ማነው ያነጋው ሌሊቱን ማነው ያጠፋው እሳቱን ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ (2x) ጌታ ምርኮያችንን ሲመልስ ለቅሶ በመዝሙር ሲተካ ቃላችን ውስን ምድራዊ ደስታችን በምን ይለካ አፋችንን በሳቅ ሞላ አንደበታችን ምሥጋና ሁሉን ውብ አድርጓል የታሪክ ጌታ ነውና (2x) አዝ፦ ማነው ያነጋው ሌሊቱን ማነው ያጠፋው እሳቱን ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ነው ክንደ ብርቱ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection