አዝ፦ ዓለም ሁሉ በሽተኛ ሕመምተኛ ግን መድሃኒት አለን እኛ ኑ ወደ እኛ ሥሙ ኢየሱስ መድሃኒ ዓለም እንደርሱ ያለ የትም የለም ፀንቶ የሚኖር ለዘለዓለም (2x) እውነት ሕይወት መንገድ እርሱ ለነፍስ መዳን ለሥጋ ፈውሱ ድምፁን ስሙ ተመለሱ ወደ እርሱ ኑ ዛሬውኑ (2x) የኦሪት ሕግ መተኪያ የነቢያት ትንቢት መሙያ የአዲስ ኪዳን መጀመሪያ ኢየሱስ ነው ሃሌሉያ ኢየሱስ ነው ሃሌሉያ ድንግል ማሪያም ደስ ይበልሽ የአምላክ ፀጋ የሞላብሽ የማህፀንሽ በኩር ፍሬ ያድነናል እስከ ዛሬ ያድነናል እስከ ዛሬ (2x) አዝ፦ ዓለም ሁሉ በሽተኛ ሕመምተኛ ግን መድሃኒት አለን እኛ ኑ ወደ እኛ ሥሙ ኢየሱስ መድሃኒ ዓለም እንደርሱ ያለ የትም የለም ፀንቶ የሚኖር ለዘለዓለም (2x) እውነት ሕይወት መንገድ እርሱ ለነፍስ መዳን ለሥጋ ፈውሱ ድምፁን ስሙ ተመለሱ ወደ እርሱ ኑ ዛሬውኑ (2x) በባሕር ዳር በገሊላ በሞት አገር በሞት ጥላ ተወለደ ብርሃን አብሪ የአስጨናቂውን ዘንግ ሰባሪ የአስጨናቂውን ዘንግ ሰባሪ የአስጨናቂውን ዘንግ ሰባሪ ሕፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነት በጫንቃው ላይ እልል በሉ ምድር ሠማይ እልል በሉ ምድር ሠማይ (2x) አዝ፦ ዓለም ሁሉ በሽተኛ ሕመምተኛ ግን መድሃኒት አለን እኛ ኑ ወደ እኛ ሥሙ ኢየሱስ መድሃኒ ዓለም እንደርሱ ያለ የትም የለም ፀንቶ የሚኖር ለዘለዓለም (2x) እውነት ሕይወት መንገድ እርሱ ለነፍስ መዳን ለሥጋ ፈውሱ ድምፁን ስሙ ተመለሱ ወደ እርሱ ኑ ዛሬውኑ (2x) ሳይጠበው ምድርን ሳይሞላ ሰው እርስ በእርሱ የሚባላ ጦር የሚመዝ በወንድሙ ፈውስ አጥቶ ነው ለሕመሙ ፈውስ አጥቶ ነው ለሕመሙ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ ደግሞም የዘለዓለም አባት ስሙም የሰላም አለቃ እርሱን ብንይዝ ችግር በቃ እርሱን ብንይዝ ችግር በቃ (2x) አዝ፦ ዓለም ሁሉ በሽተኛ ሕመምተኛ ግን መድሃኒት አለን እኛ ኑ ወደ እኛ ሥሙ ኢየሱስ መድሃኒ ዓለም እንደርሱ ያለ የትም የለም ፀንቶ የሚኖር ለዘለዓለም (2x) እውነት ሕይወት መንገድ እርሱ ለነፍስ መዳን ለሥጋ ፈውሱ ድምፁን ስሙ ተመለሱ ወደ እርሱ ኑ ዛሬውኑ (3x) ፈውስ በሌለው በሽታ ዓለማችን ስትመታ ሰው እንደ እቃ የትም ሲጣል ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ የምስራች ላብስራችሁ መድሃኒቱን ልንገራችሁ ኢየሱስን እንቀበል አንሰቃይ እፎይ እንበል አንሰቃይ እፎይ እንበል (2x) አዝ፦ ዓለም ሁሉ በሽተኛ ሕመምተኛ ግን መድሃኒት አለን እኛ ኑ ወደ እኛ ሥሙ ኢየሱስ መድሃኒ ዓለም እንደርሱ ያለ የትም የለም ፀንቶ የሚኖር ለዘለዓለም (2x) እውነት ሕይወት መንገድ እርሱ ለነፍስ መዳን ለሥጋ ፈውሱ ድምፁን ስሙ ተመለሱ ወደ እርሱ ኑ ዛሬውኑ (5x)