አዝ፦ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ በዛና እንቆቅልሼ ለብዙ ዘመን አልቅሼ አንድ ቀን ዝናህን ሰማሁ ልነግርህ ከሳባ መጣሁ ተቀመጥ በዙፋንህ የልቤን እንድነግርህ አዝ፦ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ በግመል ሽቱ ጭኛለሁ ወርቅናዕንቁም ይዣለሁ ደክሞኛል ጓዜ ብዙ ነው አድምጠኝ ያኔ አርፋለሁ አገሬን በዚህ ወክዬ ከእግርህ ስር ልውደቅ ጌታዬ አዝ፦ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ ሠማይና ምድርን ፈጥረሃል በጥበብህ ሁሉን አድርገሃል ከዓይንህ የተሰወረ አሸንፎህስ የኖረ ንጉሥ ሆይ ኧረ ምን ነበር ፍታልኝ የእኔንም ነገር አዝ፦ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ ገና ጥንት ሳለሁ በአገሬ ስለ አንተ የሰማሁት ወሬ ማመን ግን አቅቶኝ ነበር ልክ የለው የዕውቀትህ ነገር ጥበብህ ከአእምሮ ያልፋል ከሰማሁት ዝናህ ይበልጣል አዝ፦ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዙ እንቆቅልሽ አለኝ ጌታ አንተ ንጉሥ ነህ እንቆቅልሽን መፍታት ታውቃለህ የዕውቀት የጥበብ ጌታ እንቆቅልሼን ፍታ