Song Lyrics

ከኢየሱስ ጋር ኑሮ

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Genana New
ሕይወት እንደ ጥላ ሲያልፍ ውበት እንደ ቅጠል ሲረግፍ ያመኑበት ወዳጅ ሲከዳ ከኢየሱስ ጋር ሆኜ ልጐዳ አዝ፡- ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል (2x) ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል አክሊል ከምደፋ በዓለም የኢየሱስን መስቀል ልሸከም ሰይጣን ከሚያቆላምጠኝ ኢየሱሴ በእግሩ ይርገጠኝ አዝ፡- ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል (2x) ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል ዙሪያዬን አጅቦኝ ወታደር በቄሳር ሰገነት ከማደር ደም እንባ እያፈሰስኩ ለጌታ ይሻለኛል ለእኔስ ጐልጐታ አዝ፡- ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል (2x) ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል በረደኝ አልልም ከንግዲህ ራበኝ ጠማኝ አልል ከንግዲህ አፌን በአፈር ውስጥ ቀብሬ እኖራለሁ ቃሌን አክብሬ አዝ፡- ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል (2x) ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይሻለኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection