Song Lyrics

ምሥጋና

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Genana New
ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ አሳዳጃችን ከባሕር ሰጥሞ ምድረ በዳችን በአንተ ለምልሞ ከያለንበት ተሰብስበናል እኛም ሰው ሆነን ሰውን ማርከናል አዝ፡- ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ከአእምሮያችን በላይ ለሆነው ውለታህ ቆጥረን እስከማንዘልቅ ለበዛው ስጦታህ እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ በሰው ልጅኀጢአት ምድርንብትቀጣ የመከራ ጐርፍ ከላይ ቢመጣ በዙሪያችን አጥር ሰርተሃል ለእኛ ለሕዝብህ መርከብ ሆነሃል አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ከአእምሮያችን በላይ ለሆነው ውለታህ ቆጥረን እስከማንዘልቅ ለበዛው ስጦታህ እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ የፈርኦን ጦር ሕዝቡን አሳዶ እርሱ ግን ቀረ ከባሕር ማዶ እርስታችንን በድል ወርሰናል በአንተ እረኝነት እዚህ ደርሰናል አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ከአእምሮያችን በላይ ለሆነው ውለታህ ቆጥረን እስከማንዘልቅ ለበዛው ስጦታህ እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection