Song Lyrics

ኢየሱስ ገናና ነው

Pastor Tamrat Haile
Eyesus Genana New
ክብሩን ሁሉ ትቶ ከሠማይ ወረደ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና የሰው ሥጋ ለብሶ ራሱን አዋረደ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና የእግዚአብሔር በግ ሆኖ . (1) . ተወለደ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና የዋህ ትሁት ሆኖ እንደ በግ ታረደ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ፈራጅ በሌለበት እውነተኛ ዳኛ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና የውርደት ሞት ሊሞት እንደወንጀለኛ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በደሙ ቢነከር ቀራንዮ ተራራ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና መቃብሩም ቢሆን ከአመፀኞች ጋራ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በሞተ ሰልስቱ ታሪክ ተለወጠ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አይሰማ ሰምቶ ዓለም ደነገጠ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና መቃብሩን ከፈተ ማኅተሙን ፈታ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ሞትን ድል አረገ የትንሳኤው ጌታ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አዝ፦ ገናና ኢየሱስ ገናና (4x) ተወዳዳሪ የለውምና አቻ የሚሆነው የለውምና ገናና ኢየሱስ ገናና (3x) የሞት መርዶ ሰምተው በሃዘን የተዋጡ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በትንሳኤው ብስራት ዕልልታ አቀለጡ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አጠፋነው ብለው የዘፈኑ ሁሉ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ትንሳኤውን ሲሰሙ ምድር ዋጪን አሉ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በኢየሱስ ሰፈር ዕልልታ ሲሰማ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በዲያብሎስ ሰፈር የሃዘን ጨለማ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ከማሪያም ጀምሮ እስከ ቶማስ ድረስ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በዐይን በማየት ደግሞም በመዳሰስ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ኢየሱስ መነሳቱን አረጋገጡልን ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ይህን ክቡር ታሪክ ፅፈው አስቀሩልን ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አምነን የተቀበልን እኛም ተነስተናል ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በኢየሱስ ትንሳኤሞትን እረግጠናል አዝ፦ ገናና ኢየሱስ ገናና (4x) ተወዳዳሪ የለውምና አቻ የሚሆነው የለውምና ገናና ኢየሱስ ገናና (3x) የኢየሱስ ጌትነት በዚህ አላበቃም ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ገና ይቀጥላል ታሪክ አልተዘጋም ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ከትንሳኤው ኋላ አርባ ቀናት ኖሮ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና የቤተ ክርስቲያን መሰረት አኑሮ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ሰው ሆኖ የመጣው ጌታ ሆኖ ሄዷል ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በውርደት የመጣው በክብር አርጓል ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ዛሬም ሕያው ሆኖ በአብ ቀኝ አለልን ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና እያማለደልን ቤት እየሰራልን ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ያኔ መጀመሪያ በግ ሆኖ የመጣው ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ዳግም ሲመለስ ግን የጌታዎች ጌታ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በመለከት ድምፅ በመላእክት አጀብ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አብረን እንድንገባ ቶሎ እንመዝገብ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ስለስሙ ብለው የተገፉ ሁሉ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ኢየሱስ ሲከብር አብረው ይከብራሉ አዝ፦ ገናና ኢየሱስ ገናና (4x) ተወዳዳሪ የለውምና አቻ የሚሆነው የለውምና ገናና ኢየሱስ ገናና (3x) ዛሬም በዚህ ዘመን በሕይወቱ እያለ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ካልካደ በስተቀር ያላየ ማን አለ? ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ክህደትን አመፅን ከምድር ሲያጠፋ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና የእግዚአብሔር መንግሥት ድንበሯ ሲሰፋ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በኢየሱስ ስም ስልጣን ወንጌሉ ሲሰበክ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ምላስ ሲመሰክር ጉልበት ሲንበረከክ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ታዲያ ለምንድነው ወገኔ የምትደክም? ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ሕያው አምላክ እንጂ ግኡዝ አታመልክም ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና በዚህ አጭር ዘመኔ ኧረ ስንት አሳየኝ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ለኢየሱስ ጌትነት እኔም ምስክር ነኝ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አንቺም ምስክር ነሽ አንተም ምስክር ነህ ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና ሁላችንም እንበለው ኢየሱስ ጌታ ነው ኦ ገናና ነው ኦ ኢየሱስ ገናና አዝ፦ ገናና ኢየሱስ ገናና (4x) ተወዳዳሪ የለውምና አቻ የሚሆነው የለውምና ገናና ኢየሱስ ገናና (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection