አዝ፦ ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (2x) ከታላላቆች ከአለቆች ጋራ ፊት ለፊት ቆሜ እኩል ላወራ ስለሆንክልኝ ግርማ ሞገሴ ከፍ በልልኝ ጌታ ኢየሱሴ አዝ፦ ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (2x) አድነኸኛል ከሰቆቃዬ በአንተ መጽናናት ደርቋል እንባዬ አቁመኸኛል በተራራ ላይ አብቅተኸኛል ክብርህን እንዳይ አዝ፦ ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (2x) በአንተ ለምልሟል ምድረ በዳዬ በረከት ሞልቷል የሕይይወት ጓዳዬ ላይ ታች ከማለት ከሩጫ አርፌ መብላት ጀመርኩኝ እሸት ቀጥፌ አዝ፦ ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (2x) ዛሬስ ጠላቴ ሥፍራውን ለቋል ከላይ የነበር ከእግሬ ሥር ወድቋል በአንተ ጀግንነት ነጻ ወጣሁኝ አንተ ስትከብር እኔም ከበርኩኝ አዝ፦ ጌታዬ በአንተ ሰው ሆኛለሁና እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምሥጋና እንባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል ሐዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል (2x)