Song Lyrics

ላደረክልኝ የምመልሰው

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ ላደረግህልኝ የምመልሰው አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና በእጄ ያለው ይኸው ነውና (2x) አንደበት የለኝ ሥምህን ልጠራ ምላስም የለኝ ሥራህን ላወራ ልናገርም ብል ጊዜም አይበቃ ተመስገን ብዬ በአጭሩ ላብቃ (2x) አዝ፦ ላደረግህልኝ የምመልሰው አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና በእጄ ያለው ይኸው ነውና (2x) በፍቅር ቃልህ ልቤን ስትመታ ነፍሴን ሥጋዬን ከእስር ስትፈታ ምን አለኝና ምኔን ልክፈልህ ከተቀበልኸኝ ክበር ልበልህ (2x) አዝ፦ ላደረግህልኝ የምመልሰው አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና በእጄ ያለው ይኸው ነውና (2x) ከትቢያ አንስተህ ሰው ስታደርገኝ በነፍስ በሥጋ ስትባርከኝ ሰማያዊ ፍቅርህ ልቤን ሲሞላ ተመስገን እንጂ የለኝም ሌላ (2x) አዝ፦ ላደረግህልኝ የምመልሰው አንዳች የለኝም እጄም ባዶ ነው እንካ ተቀበል የአፌን ምሥጋና በእጄ ያለው ይኸው ነውና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection