Song Lyrics

በዚህ ዘመን

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (2x) ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል ኃጥያት በትር ይዞ ኦሆሆ አደባባይ ወጣ አሃሃ የሚቃወሙትን እኽኽ በችጋር ሊቀጣ አሃሃ ክፉዎች ሲደላቸው ኦሆሆ ጻድቃን ሲቸገሩ አሃሃ ተገለባበጠ እኽኽ እንዴት ነው ነገሩ አዝ፦ በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (2x) ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል ሃሰት ሲደራርብ እኽኽ በሹመት ላይ ሹመት አሃሃ እውነት ተናጋሪ እኽኽ ጠላት ሲበዛበት እኽኽ ደሆች ሲነቀሉ ኦሆሆ ከቤትከርስታቸው እኽኽ ጻድቅ ፈራጅ አምላክ አሃሃ ተሟገትላቸው አሃሃ አዝ፦ በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (2x) ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል አውሬው ሲያቆጠቁጥ እኽኽ ሥሩን ሲዘረጋ አሃሃ ሃሰተኛው መሲሕ እኽኽ አጃቢ ሲያንጋጋ አሃሃ ጊዜውን ካልመረመርን ዘመኑን ካልዋጀን አሃሃ የተወሰድን እንደሆን ኦሆሆ ሰዎች ምን ሊበጀን አሃሃ አዝ፦ በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (2x) ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል መዝናናት አበዛን እኽኽ መዋጋት ትተናል አሃሃ ያለነው ጦር ሜዳ አሃሃ መሆኑን ረስተናልእኽኽ እስኪ እንበርከክ እኽኽ ወደ እልፍኝ እንግባ እኽኽ ሰይጣን ጸሎት እንጂ አሃሃ አይፈራም ጭብጨባ አሃሃ አዝ፦ በዚህ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላሉ (2x) ጌታ ሆይ አብዛልን ማስተዋል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection