አዝ፦ ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች አሉ በዙሪያችን እኛም ደግሞ ሃያል ክንድህ ድንቅ አድርጐ አይተናል በዓይናችን እግዚአብሔር ታላቅ ነህ ከምንልህ በላይ ሥምህ ብሩክ ይሁን በምድር በሰማይ (2x) አዝ፦ ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ በነፍሳችን እንዳንዝል እንዳንደክም ደግፎ የሚያቆመን ለአንድ አፍታም የማንረሳው የማንጥለው ድንቅ ታሪክ አለን የነገው ደመና የሚያጨልመው ነገር አይከለክለንም አንተን ከማመስገን (2x) አዝ፦ ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ አይተንሃል ሰምተንሃል ዳሰንሃል እንመሰክራለን እንደ ጠላታችን ምኞት አልጠፋንም ዛሬም በሕይወት አለን በሆነልን ነገር ብዙ ተደንቀናል የአባታችን መንግሥት ገና ይጠብቀናል (2x) አዝ፦ ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ ጻድቅ ፈራጅ እውነተኛ ፊትን አይተህ ፈጽሞ አታደላ ፀሐይ ለጠለቀችበት ለጨነቀው ትሰጣለህ መላ ጊዜ ደረሰና ሁሉም ልኩ ታውቋል የሳቀ ሲያለቅስ ያለቀሰም ስቋል (2x) አዝ፦ ባነበብነው በሰማነው ብቻ መች ሆነና የተከተልንህ ሕያው ምስክር ነን እኛም አየንህ