Song Lyrics

አውርቼ አልጨረስኩም

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
ለአሉባልታ ጊዜ የለኝ እኔ አውርቼ አልጨረስኩ ስለመዳኔ አልጣላ ሁሉም የመጣው ከአንተበኋላ በመቦጫጨቅ ባርኮት አይመጣ ለውኃ ጥማት ወሬ አይጠጣ እስኪ እንጨብጥ እርፍ ማረሻ ሥራ ነውና የአገር መነሻ አሀ አሀ አርሰን ሳንዘራ መስከረም ጠባ አገር በወሬ አትገነባ ነገም እንዳያልፍ እንደ ትላንቱ ይሻል መሰለኝ ጎበዝ መንቃቱ ከአየር ከውሃው ምንም አላጣን ስላልሰራን ነው ረሃብ የቀጣን የሞተው ሞቶ ያለነው አለን ታጥቀን ከወጣን ነገ እንደርሳለን አሀአሀ መስመር ጠብቆ ሮጦ ማሸነፍ ወይስ በተንኮል ወንድምን መጥለፍ የትኛው ይሆን የተፈቀደው እኔ ትቻለሁ ህሊና ይፍረድ እጣ የደረሰው ትላንት ተገፋ ዛሬስ ማን ይሆን ባለወረፋ እግዚአብሔር ሆይ እየን ከሰማይ የፍቅር ዘይት አፍስስ በእኛ ላይ የወሬ ጠላት ሥራን አፍቃሪ በውኃ በየብስ በአየር በራሪ የትውልድ ኩራት መድሃኒተኛ አምላካችን ሆይ አምጣልን ለእኛ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection