Song Lyrics

ምድር ሰፊ ናት

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x) የፍቅርን ጌታ እያመለክን የፍቅርን ወንጌል እየሰበክን መኖር ስንችል ተዘልለን ጠላት በዘዴ ሥራ ሰጠን ፍቅርን አሳዶ ጥልን አንግሶ በዓለም መድረክ ወንድሙን ከሶ ቢያዜም ቢጸልይ እንዳይቀር ወጉ ማን ተባረከ እስኪ ፈልጉ አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x) የራሱን ሰርቶ የሌላውን ሊያፈርስ አንዱ በሌላው ከንፈሩን ሲነክስ ጠላት ከኋላ ድንበር ሲገፋ አርቆ አሳቢ አስተዋይ ጠፋ ጌታ ኢየሱስ የሞተላቸው በጐቹ ሁሉ የእርሱ ናቸው በማን ርስት ነው የምንጣላው እንመለስ ፍርድ አለ ኋላ አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x) በአንድ ቤት ማደር ቢያቅታቸው አብርሃምና ሎጥ ቤተሰብ ናቸው ችለው የለም ወይ ግራ ቀኝ መሄድ ከማን ተማርነው ወገን ማሳደድ ለምንኖርባት ለዚህች ምድር ተስፋዋ ማነው ያለእግዚአብሔር ፍቅርና ብርሃን በእኛ ከጠፋ በቃ አለቀላት የላትም ተስፋ አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x) ፍቅር ርቦናል ፍቅር ጠምቶናል ነገር ክርክር አንገላቶናል እናንት አባቶች ፍቅርን መግቡ ከተስፋው አገር በሰላም አግቡ አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection