Song Lyrics

ጌታ ተባረክ

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ ጠራኸኝ ከዚህ ክፉ ዓለም ነፍሴን አዳንካት ለዘለዓለም ከዚህ የበለጠ ደስታ ምንም የለም ይኸው ሞላልኝ ስለቴ ክበር ከፍ በል በህይወቴ ለአንተ ክብር ይዋል መላው እኔነቴ አዝ፦ ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ በክቡር ደምህ አንጽተህ በመንፈስ ቅዱስ ቀብተህ አገልጋይ አረግኸኝ ጸጋን ከላይ ሞልተህ ለስምህ ክብር ልዘምር በምሥጋና ላይ ልጨምር ላቆምኸኝ ላምላኬ ይሁን ለአንተ ክብር አዝ፦ ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ ጠላት ቢነሳ በአመጻ ቢወረውርም ፍላጻ ቆምኩኝ እስከዛሬ ከአንተ የተነሳ ክረምት ከበጋ አለፈ ቃልኪዳንህ መች ታጠፈ አንተን በእኔ ላይ ሲያይህ ሁሉም ተሸነፈ አዝ፦ ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ የሶሪያ ንጉሥ ደማስቆ ሴራ ተንኮሉን ማን አውቆ አልሞ ነበር ሊይዘኝ አሾልቆ አንተ ግን አታጣ መላ ለባሪያህ ሆንኸኝ ከለላ አተምከው ዙሪያዬን በእሳት ሰረገላ አዝ፦ ጌታ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ አባት ተባረክ ወዳጅ ተባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ይንበርከክ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection