Song Lyrics

እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው እንዲህ አለው (3x) አንተ ተራራ ! ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ? በዘሩባቤል በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ አለው (3x) ናደው ደለደለው ከእንግዲህስ ምን ሊበጀኝ እየየ ማለት ሰለቸኝ አይደርሰኝም ወይ ወረፋ አይገድህም ወይ ስጠፋ አምላካዊ መልስ ከሰማይ ዘሎ በኮረብታዎች ላይ ዙሪያ ገባውን አበራው ተገፈተረ ተራራው አዝ፦ እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው እንዲህ አለው (3x) አንተ ተራራ ! ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ? በዘሩባቤል በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ አለው (3x) ናደው ደለደለው የኖራ ሜዳ ሃውልቱ ሰባት እጥፍ ነዶ እሳቱ ሊያጠፋኝ የተመኘው ጌታ በቁጣው ጐበኘው ጠላት ለራሱ ቆፈረ ሊያስረኝ የወጣው ታሰረ ሊበላኝ ያሻው ለራሱ ተበላ እኔ ግን አለሁ በተድላ አዝ፦ እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው እንዲህ አለው (3x) አንተ ተራራ ! ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ? በዘሩባቤል በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ አለው (3x) ናደው ደለደለው የብዙ ዘመን ጠላቴ ቆሞ የነበረው በፊቴ ብርሃን እንዳላይ ከልሎ አየሁ በጌታዬ ተጥሎ ጌታ በሰራው ከበረ መዝሙር በአፌ ጨመረ ሰማይ ያጨብጭብ በደስታ ምድር ታክብረው በእልልታ አዝ፦ እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው እንዲህ አለው (3x) አንተ ተራራ ! ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ? በዘሩባቤል በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ አለው (3x) ናደው ደለደለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection