Song Lyrics

ጌታዬን ያገኘሁ ቀን

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን ሃይማኖት አለኝ ስል ስገበዝ ከርሜ (2x) መጠውለጉን ሳላውቅ ቅጠል አገልድሜ (2x) እርቃኔ ሲገለጥ እፍረት ያዘኝና (2x) ወደ ጌታ ሮጥኩኝ መሃሪ ነውና አዝ፦ የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን ሰው በእህል አይጠግብም ውሃም አያረካው (2x) የእግዚአብሔር ቃል በፍቅር ካልነካው (2x) ጤና ነኝ እያለ እራሱን ያስታል (2x) ቀን ቀን በሳቀበት ማታ ያቃስታል አዝ፦ የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን ታሪክ ያለኝ ይመስል በከንቱ ስኮፈስ (2x) ቀራንዮን ትቼ ታቹን ስመላለስ (2x) ጫማዬን ስጨርስ በሸለቆ ድንጋይ (2x) የመለኮት ጥሪ መጣልኝ ከሰማይ አዝ፦ የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን አልጋዬ ቆርቋሪ እንቅልፍ የማይሰጠኝ (2x) ምንድነው እንደዚህ የሚያገላብጠኝ (2x) እያልኩኝ ስመረር ኢየሱስ ደረሰ (2x) የሰላም አሸንዳ በላዬ አፈሰሰ አዝ፦ የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን ቀኒቷም ትባረክ ጌታን ያየሁባት (2x) ከዘመናት እስር የተፈታሁባት (2x) የምስራች ያለኝም እርሱን ጌታ ይክፈለው (2x) ጌታ እኔን ሲሸልም ለእርሱም አክሊል አለው (2x) አዝ፦ የነፍሴን መድሃኒት ኢየሱስን እስካገኝ ሰላም አላየሁም እረፍት አልነበረኝ የመቅብዝበዝ ኑሮ ነበር የሰቀቀን ታሪክ ተለወጠ ጌታን ያገኘሁ ቀን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection