Song Lyrics

ድካሜን አንሳ ከላዬ

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Terarayen Anagerew
አዝ፦ አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (2x) ግብረ ጉንዳን መኖዋን በበጋ አሰናድታ ክረምት በመጣ ጊዜ ትበላለች ተኝታ ጻድቅ በምቹ ጊዜ በአንተ ፊት ከተጋ ዋስትና አለውና ይኖራል ምንም ሳይሰጋ አዝ፦ አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (2x) ካልተጠበቀ መንጋ ማነው ወተት የሚሻ? ያልዘሩትን ለማጨድ አይኬድም ወደ እርሻ ጥያቄ በመጣ ጊዜ እምነቴ እንዳይከዳኝ ዛሬ ቀን ሳለ ጌታ ፍቃድህን ልፈጽም እርዳኝ አዝ፦ አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (2x) ትጥቄን ሳላጠባብቅ እንዲያው መሮጥ ካሰኘኝ ተጠልፌ ወድቄ ጠላት እንዳያገኘኝ ዛሬ ስራኝ በጓዳ በአደባባይም አይደል ኋላ አያቅተኝም በአንድ ጠጠር ሺህ መግደል አዝ፦ አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (2x) ከተከፈተ ሰማይ ወርቃማ ቅባት ፈሶ ጸጋህ በውስጤ ይሙላ መንፈሴን አረስርሶ ደዌን እገስጻለሁ መናፍስትን አዛለሁ ጭፍሮችን አባርሬ ምርኮን እበዘብዛለሁ አዝ፦ አቤቱ ድካሜን አንሳ ከላዬ ኃይልን አልብሰኝ ጌታዬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection