Song Lyrics

እግዚአብሔር ይባርክህ

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Awaki New
በአንድነት አስሮ በፍቅር ባርኮ ይስብስብልህ ምርኮ በምርኮ ብዛ ተባዛ የአባቴ መንጋ ይሚነሳብህ ወገብ ይወጋ አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ የጽድቅን ኑሮ የቅድስናን እያበዛልህ ጸሎት ጽሞናን የቃሉን ረሃብ የአምልኮን ጥማት ያትረፍርፍልህ ቅባት በቅባት አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ ሽማግሌዎች ከአደባባይ ህጽናት ልጆች ከሜዳው ላይ የአዝመራው መዓዛ የአምልኮ መድረክ ሁሉም ይለምልም ሁሉም ይባረክ አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ የግብጽ ቁስል ደዌ ቸነፈር ጭንገፋና ሞት አንተን አይድፈር ቀሳፊው መልአክ ቤትህ አይግባ ጉበን መቃንህ በደሙ ይቀባ አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ ተምች አይውረር ደግሞም ኩብኩባ የአየር ንብረትህ እንዳይዛባ ወንዝ አፈርህ ጌታ ይባርክልህ ቁርባን መስዋዕትህን ያለምልምልህ አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection