Song Lyrics

አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Awaki New
በእንባና በጣር በጭንቅ በመከራ በእሳት ውስጥ አልፎ ሕይወቴ ተገራ ማዕበሉም ንፋሱም ሰራኝ ደህና አድርጎ ጠላት ለክፉ ሲል ሆነልኝ ለበጐ ዛሬማ ወዳጄ ዐይኖቼ ተከፍተው አያለሁ አርቄ የሕይወት ትርጉሙ በወጉ ገብቶኛል 'ይዛለሁ አጥብቂ አድራሻዬን አዝ:- አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (2x) መዳኛዬ መጽናኛዬ መፈወሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ የብሶት የቋቱም ሲገነፍል ሞልቶ እምነቴ ሲከዳኝ መታጠቂያው ላልቶ የመለወጫዬ የጸሎቴ ቦታ ድምጹን ሲያሰማኝ ሲያናግረኝ ጌታ እጁ ስትዳስሰኝ ሸክሜን ሲያወርድልኝ ሁሉን እረሳለሁ በሃዘን መጥቼ በእምባ ተንበርክኬ በሳቅ እነሳለሁ አድራሻዬ አዝ:- አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (2x) መዳኛዬ መጽናኛዬ መፈወሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ ንፋሱ ባይነፍስ ባይታይ ደመና እጠብቀዋለሁ ጌታ ብሏልና ቃሉ አይታጠፍም ታማኝ ነው አምላኬ ምስክር ቢያስፈልግ የትላንት ታሪኬ የመጠበቂያዬን የጸሎቴን አምባ አልወጣም ለቅቄ እስቲ መልስልኝ እማጸነዋለሁ ከእግሩ ስር ወድቂ አድራሻዬ አዝ:- አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (2x) መዳኛዬ መጽናኛዬ መፈወሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ ያወቀ ይስታል የቆመም ይወድቃል ብልህ ሰው ለነገ ስንቁን ይሰንቃል የጭንቀቱ ጭጋግ የተስፋውን ጮራ ሲሸፍነው ዋለ ወሬ ስናወራ አሁን ይበቃናል ለወሬ በርክተን ለጸሎት መስነፉ እንግባ ከጓዳ እዚያ ነው ሚገኘው የበረከት ቁልፉ አድራሻዬ አዝ:- አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (2x) መዳኛዬ መጽናኛዬ መፈወሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection