Song Lyrics

የለብኝ ኩነኔ

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Awaki New
ካህኑ እያሱ ቢቆሽሽም ልብሱ ቢጠፋው ውበቱ ቢደክም ጉልበቱ አምላኩ አልተወውም አልቆበት ምህረቱ የጠላትን ምኞት አደረገበት ከንቱ ሰይጣን ቢከሰውም እያብጠነጠነ ሳር እየበተሰ ስር እየነቀለ ከሳሽም እራሱ ምስክር እራሱ ጌታ በቀባው ላይ ሲያስረዝም ምላሱን የተሰየመውን ከችሎቱ መሃል ቀና ብሎ ቢያየው የእርሱ አምላክ ኖሯል እኔ አልፈርድበትም ይሂድ ወደ ቤቱ ከስልጣኑ አይውረድ ይቀጥል ክህነቱ ተቀብዬዋለሁ ከነ ማንነቱ የጠላትን ምኞት አድርጊያለሁ ከንቱ ያዳም ዘር አፈር ስጋ ሰው መሆኑን ሳልዘነጋ የጠራሁን በእኔ ጸጋ ዋጋው አለ ከእኔው ጋር ይልቅ እድፋሙን ልብስ አውልቁለት ቶሎ መሸማቀቁ ይቅር ይሂድ ቀና ብሎ የክት ልብስ ይልበስ ከእግር እስከራሱ ከእንግዲህ ነጻ ነው ተፈቷል እያሱ አዝ:- በክርስቶስ ኢየሱስ ስራ በማመኔ የለብኝ የለብኝ የለብኝ ኩነኔ (2x) ቃሉ እንደሚናገር ጥንት በኦጽ አገር እዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበር ፍፁምና ቅን ነው ከክፋት የራቀ አምላኩን ሚፈራ አመጽ ያላወቀ በልጅና በሃብት መባረኩን አይቶ ያሳጣው ጀመረ ቀናተኛው ቀንቶ ክሱን አዘነበው በራሱ እየማለ ስለባረከው ነው የፈራህ እያለ እስቲ የዙሪያውን አጥሩን አፍርስበት እጅህን ዘርጋና ያለውን ንካበት ያኔ ይሰድብሃል አንደበቱን ከፍቶ ማነው የሚታገስ ሃብቱን ተቀምቶ እያለ ቢከሰው ሃሰትን ቀምሞ እዮብ ድል አደረገ በእምነቱ ቆሞ ወዶ ሰጠኝ እግዚአብሔር ለምሥጋናው ለእርሱ ክብር ደግሞም ወዶ ከወሰደው አይጠየቅ ስልጣኑ ነው መልካሙን እንዳየ ክፉን ብንቀበል ሥሙ ብሩክ ይሁን ምሥጋናው ከፍ ይበል ሁለት እጥፍ ክሶ እግዚአብሔር ፈረደ እዮብ በድል ወጣ ከሳሽ ተዋረደ አዝ:- በክርስቶስ ኢየሱስ ስራ በማመኔ የለብኝ የለብኝ የለብኝ ኩነኔ (2x) እኔን ደስ ሲለኝ ጠላቴ ከፍቶታል መባረኬን ሲያይ እሳት ሆኖበታል ምክሩ ፈረሰበት አልሆነ እንዳሰበው እኔም ድሌን ላውጅ ጨምሮ ያንገብግበው መልካሙን ስራውን በእኔ የጀመረው ይፈጽምልኛል ጌታዬ ታማኝ ነው ሰይጣን ዘዋሪ ነው ሁሉን ያዳርሳል መክሰስ ልማዱ ነው ማንንም ይከሳል የክርስቶስን ደም ዋጋ አሳንሶ ከወንጌሉ ተስፋ ግማሹን ቀንሶ በተንኮል ሽንገላው እይተታለልን ሶኮነን ሲከሰስ ስንቱ ከቤት ዋለ ዘወትር የሚሸከም ጉድለት ድካምህን በሰማያት አለ ታላቅ ሊቀ ካህን እኔም ሆንኩኝ አንተም አንቺ ለሰይጣን ክስ አትመቺ አለንና ዋስ ጠበቃ ለሁላችን የሚበቃ ከእምነት አናፈግፍግ እንታመን እንጂ አለን በሰማያት ጽድቅ አማላጅ ሙሉ ዋጋ ከፍሎ በጸጋው አድኖኛል ሁሉን አሳልፎ ጽዮን ያገባኛል አዝ:- በክርስቶስ ኢየሱስ ስራ በማመኔ የለብኝ የለብኝ የለብኝ ኩነኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection