Song Lyrics

ሰው ከንቱ

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Awaki New
እንገናኝ ነገ እንገናኝ ደህና ዛሬን ለማደሩ መች አወቀውና ሰው ከንቱ (2x) መንገዱን ሲያረዝም እቅዱን ሲያሰፋ ዘንግቶት ይሆናል ታይቶ እንደሚጠፋ ሰው ከንቱ (2x) አዝ:- ሰው ከንቱ (6x) ጌታ ብቻ ብርቱ (2x) ጀግና ወጥቶ ሲቀር ጐበዙ ሲቀጠፍ ነገን እያሰቡ ከዛሬ ዓለማለፍ ሰው ከንቱ (2x) ብዬ ጠጪ እያለ ነፍሱን ሲያዝናና ሞት እንደ ደራሽ ወንዝ ድንገት ይመጣና ሰው ከንቱ (2x) አዝ:- ሰው ከንቱ (6x) ጌታ ብቻ ብርቱ (2x) ይህ ለእኔ ያ ለእኔ እዚም እዚያም እኔ ካለው ካገደመው ሲቅበዘበዝ ዐይኔ ሰው ከንቱ (2x) የነኤገሌ ዘር ነኝ ሃብቴም እንዳፈር ማንና ምን ይሆን አብሮኝ የሚቀበር ሰው ከንቱ (2x) አዝ:- ሰው ከንቱ (6x) ጌታ ብቻ ብርቱ (2x) በውበት መመካት ዕውቀት አለኝ ማለት ህልም ሆኖ ሲቀር ከአፈር የገቡ እለት ሰው ከንቱ (2x) አስተዋይ ከዛሬ የነገን ይመርጣል እግዚአብሔርን ማወቅ ከሁሉን ይበልጣል ሰው ከንቱ (2x) አዝ:- ሰው ከንቱ (6x) ጌታ ብቻ ብርቱ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection