አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (2x) በመላክት እየታጀበ በእግዚአብሔር መለከት ኢየሱስ ይመጣል ከላይ ከሰማያት የአባቴ ብሩህ ቃል ኑ እረፉ ይለናል እንደ ድካማችን ዋጋ ይከፍለናል ተስፋ እንደሌላችሁ ፈጽሞ አትዘኑ እርስ በእርሳችሁም በዚህ ቃል ተጽናኑ አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (2x) በጌታ የሞቱ ቀድመው ይነሳሉ ሰማያዊ አካል ፈጥነው ይለብሳሉ እኛ ሕያዋን እንለወጣለን አብረን በደመና እንነጠቃለን ተስፋ እንደሌላችሁ ፈጽሞ አትዘኑ እርስ በእርሳችሁም በዚህ ቃል ተጽናኑ አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (2x) ዓለም በክፋቷ እየባሰች ሄደች ሕያዋንን አልፋ በድን አሳደደች አዲስ ነገር የለም ነው እንደተጻፈው በክርስቶስ ትዕግስት ሁሉን እንለፈው የሚረዳን ጸጋ ጌታ ይሰጠናል ኋላም በመምጣቱ በክብር ይገልጠናል አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (2x) ጌታ የሚዘገይ መስሎ ቢታያቸው በዚህ ዓለም አምላክ ታውሮ ዐይናቸው እንደ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም በእውነት እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል በድንገት የወጉት ያዩታል በዘውድ አሸብርቆ በግርማው ሲገለጥ ከከዋክብት ደምቆ አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (2x) ነቀፋና ስድብ ስደትና ዛቻ የጠላት ተግዳሮት የዘመድ ጥላቻ እጦትና ህመም ሃዘንና እሮሮ ያለው የሚመጣው ሁሉም ተደምሮ ይገለጥ ዘንድ ካለው ሰማያዊ ክብር ያሁን ዘመን ስቃይ አይወዳደር አዝ:- ለጥቂት ጊዜ በልዩ ልዩ መከራ እናልፋለን በቀኑ መጨረሻ የክብርን አክሊል እንደፋለን (2x)