ወዳጄ አብርሃም ፊቴ ተመላለስ እኔን አይገደኝም ኪዳኔን ለማደስ እድሜህ ሮጦ ሮጦ ቢደርስልህ ከጫፍ ሰላም ምድር ያልፋል የኔ ቃል አያልፍም አዝ:- ታማኝ (3x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (2x) የማያልፍ ምን አለ እግዚአብሔር ከረዳ የእምነት ምንጭ ይሆናል ይሄ ምድረ በዳ ያለው ይሄድና ደግሞ ይመጣል ሌላ ግዙፉ ተራራ ይሆናል ደልዳላ አዝ:- ታማኝ (3x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (2x) የመለኮት አዋጅ ከመጣ ከሰማይ ኢየሱስ ካዘዘ ይኬዳል ውኃ ላይ ሙታን ይነሳሉ እስራት ይፈታል ቁራሹ ተባርኮ ሺሆች ይበሉታል አዝ:- ታማኝ (3x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (2x) ጌድዮንና ብርቅ ዮፍታሄና ሳምሶን ሳሙኤልና ዳዊት ጳውሎስና ጴጥሮስ የአንበሳን አፍ ዘጉ እሳት አልበላቸው ለታማኝነቱ ምስክሮች ናቸው አዝ:- ታማኝ (3x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (2x) ምድያም በረሃ በፀሐይ ቃጠሎ በቁጥቋጦ እሳት ራዕይ አቀብሎ የፈርዖንን ክንድ በመቅሰፍት አድቅቆ አሻግሮ የለም ወይ ህዝቡን አስለቅቆ አዝ:- ታማኝ (3x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (2x) ጉድጓዱን ቆፍረህ ውኃ ስታወጣ ዞርበል የኔ ነው ባይ ምቀኛ ቢመጣ እልፍ ብለህ ቆፍር ከሰው አትጣላ ርሆቦት ይሆናል የኋላ የኋላ አዝ:- ታማኝ (3x) ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (2x)