Song Lyrics

የታደለ ምስጉን ነው

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Awaki New
የሉም ሲባል ይኖራሉ (አሁሁሁ) ጠፉ ሲባል ይበዛሉ (ኦሆሆሆ) ሲዋለዱ ብዙ መንታ (አሃሃሃ) ሩጫቸውን ማን ሊገታ (አሃሃሃ) አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም ይበረታሉ እንደ ንስር ይበራሉ እጥፍ ድርብ ያፈራሉ አዝ:- እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ ዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ የታደለ ምስጉን ነዉ በሰው ብልሃት የተሰራ (አሃሃሃ) በሥጋ ደም የሚመራ (አሃሃሃ) ሃስቡን ለፍልስፍና (አሃሃሃ) እምነታቸው መች ሆነና (አሃሃሃ) ይናገሩ ያዳናቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት ናቸው ዲያቢሎስም ያውቃቸዋል ጊዜ ስጡኝ ይላቸዋል አዝ:- እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ ዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ የታደለ ምስጉን ነዉ እሳት አለ በውስጣቸው (እሄሄው) ማንም አይችል ሊያጠፋቸው (እሄሄው) አይቻሉም ሲነኳቸው (እሄሄው) ተዋጊ ነው አምላካቸው (እሄሄው) ሰባኪዎች በመገለጥ ለዲያቢሎስ እሳት ረመጥ ዘማሪዎች በበገና ይቀባሉ ገና ገና አዝ:- እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ ዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ የታደለ ምስጉን ነዉ ሰይፍ አይዙም በእጃቸው (እሄሄው) የመንፈስ ነው መሳሪያቸው (እሄሄው) እዩት እስቲ ይህን ምርኮ (ኦሆሆሆ) መንገደኛ አይደለም እኮ (ኦሆሆሆ) የክርስቶስ ስም ያዳነው የካህናት መንግሥት ነው የዓለም ብርሃን የምድር ጨው እንደ ከዋክብት የተረጨው አዝ:- እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ ዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ የታደለ ምስጉን ነዉ ሟርት አይሰራም በእስራኤል ላይ (አሃሃሃይ) አስማት የለም በያዕቆብ ላይ (ይሄሄሄይ) አይቆጠርም ብዛቱ (ዑሁሁሁ) ድንበር የለው ለግዛቱ (ዑሁሁሁ) እግዚአብሔር እፍ ያለበት የፈጠረው ለበረከት መድሃኒት ነው መፈወሻ ወሰን የለው መጨረሻ አዝ:- እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ ዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ የታደለ ምስጉን ነዉ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection