Song Lyrics

ክብር ይሁንለት

Pastor Tamrat Haile
Egziabher Awaki New
ቃሉ ሲያስተምረን መንፈሱ ሲያጽናናን ካቻምናን አለፍን ተሻገርን አምናን ጠላት ቢቃወመን እጅግ ተገዳድሮ ጌታ ተዋግቶልን ደረስን ዘንድሮ (2x) አዝ፦ ተራራ የሚናድለት ጨለማ ሚገፈፍለት ንፋሥም የሚገዙለት ወጀቡ ሚታዘዝለት ኢየሱስ ኢየሱስ ክብር ይሁንለት መጻተኞች ብንሆን ምድር ያልተገባን ምንም አልጐደለን ለእኛ ከሚረባን ወላጅ እንደሌለው ልጅ አላደረገን የሁላችን አባት እግዚአብሔር ይመስገን (2x) አዝ፦ ተራራ የሚናድለት ጨለማ ሚገፈፍለት ንፋሥም የሚገዙለት ወጀቡ ሚታዘዝለት ኢየሱስ ኢየሱስ ክብር ይሁንለት . (1) . ይመጣል አካሉ ተሟልቶ እውሩ ቢመጣ ሄደ ዓይኑ ተከፍቶ ሙታን ተነስተዋል የተራቡም በሉ እጁን ከዘረጋ ይደርሳል ለሁሉ (2x) አዝ፦ ተራራ የሚናድለት ጨለማ ሚገፈፍለት ንፋሥም የሚገዙለት ወጀቡ ሚታዘዝለት ኢየሱስ ኢየሱስ ክብር ይሁንለት ሕዝቡ እንደሆነ አይቀር ተስፋውን መውረሱ ፈርዖን ለምን ነው ኃይሉን መጨረሱ ባሕር ተከፈለ በድል ተሻገሩ አንድ እስከዘለዓለም ተሰብሯል ቀንበሩ (2x) አዝ፦ ተራራ የሚናድለት ጨለማ ሚገፈፍለት ንፋሥም የሚገዙለት ወጀቡ ሚታዘዝለት ኢየሱስ ኢየሱስ ክብር ይሁንለት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection