Song Lyrics

በምሥጋና ሁሉ ላይ

Pastor Tamrat Haile
Bedibibikosh Kenu Endayalf
አዝ፦ በምሥጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ (2x) ቅዱሳን መላዕክት ሱራፌል በሠማይ ያሉ ሳያቋርጡ ዘወትር ለአንተ ይሰግዳሉ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ቁጥር የሌላቸው በቀን በማታ እንዲያበሩ የፈጠርካቸው የጥበብህ ስራ ምሳሌ ናቸው አዝ፦ በምሥጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ (2x) ደማናዎችህ እንደጥጥ የተባዘቱ ማሰሮው ሲያዘነብል በልጉ ክረምቱ የሠማይ አዕዋፍ በየዘር በየወገኑ ማን ይናገራል የዕውቀትህ ልኩ መጠኑ በየቋንቋቸው ሲያመሰግኑህ አዝ፦ በምሥጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ (2x) የምድር ፍጥረታት ሕያዋን ተንቀሳቃሾች ሰዎች እንስሳት አራዊት የባሕር አሶች ውቅያኖስ ወንዙ ሸለቆው ደኑ ተራራ አቤት ሲያስደንቅ የቃልህ የእጅህ ስራ ሁሉም በቋንቋው ክብርህን ያውራ አዝ፦ በምሥጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ (2x) በዓለም ታሪክ በዘመን በአመታት መሃል የሌለህበት ያለአንተስ የሆነ የታል ነገሥታት ሲያልፉ ኃያላን ወድቀው ሲቀሩ ድንቅ የተባሉ ግኝቶች ሲያልፉ ሲሻሩ የእኛ እግዚአብሔር አለ በክብሩ አዝ፦ በምሥጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ (2x) አቤቱ ስራህ አሳብህ ሁሉም ድንቅ ነው ከዚህ ሁሉ በላይ ሚይስደንቅ መዳናችን ነው በመጀመሪያ በአንተ ዘንድ የነበረው ቃል በድንግል ማህጸን ሰው ሆኖ መድን ተወልዷል ጨካኙን ዘንዱ በመስቀል ቀጥቅጦ አመተ ፍዳን በአመተ ምህረት ለውጦ ሁሉን ድል አድርጐ በቀኝህ ለተቀመጠው በክብር በሥልጣን ዳግመኛ ለሚገለጠው ክብር ምሥጋና ውዳሴ ይኸው አዝ፦ በምሥጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ስምህ ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ (3x) ይባረክ ይባረክ ይባረክ ይባረክ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection