Song Lyrics

ተሻገሩ ብሎ

Pastor Tamrat Haile
Bedibibikosh Kenu Endayalf
ተሻገሩ ብሎ አዞ በውኃ ሚያስበላ ኧረ እስቲ ንገሩኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሆን ወይስ ሌላ መፈጸም አቅቶት ከአፉ የወጣውን ቃል ይቅርታ ጠይቆ ወይ ረዳት ፈልጐ እርሱ መች ያውቃል ይሄ ግን የማውቀው ጀምሮ ፈጻሚ ጠላት የመጣ እንደው እራሱን አስቀዳሚ እነርሱን ተዉአቸው እኔን ያዙኝ የሚል ከአውሬም መንጋጋ በጐቹን የሚያስጥል አዝ፦ አሁንስ ተስፋዬ ማነው ድጋፍ ምሶሶዬ ማነው አለኝታ ጋሻዬ ማነው መከታ አንባዬ ማነው ማነው (3x) እግዚአብሔር ነው ለአብርሃም ተናግሮ ነግሮ ለይሳቅ አጸና ለይሳቅ ተናግሮ ለያቆብ ፈጸመ እርሱ አይዋሽምና ዮሴፍ በግብጽ ምድር ቢወርድ ቢገባም ተሽጦ የፈርዖን መንግሥት ገዢ አደረገው ስርአት ለውጦ እግዚአብሔር ደክሟል አረጀ ያለ ማነው እኔስ እስከሚገባኝ ዛሬም ኤልሻዳይ ነው የእኔ እምነት ቢፈተን ቢለዋወጥበት እግዚአብሔር ግን ታምኖ አለ እዚያው ባለበት አዝ፦ አሁንስ ተስፋዬ ማነው ድጋፍ ምሶሶዬ ማነው አለኝታ ጋሻዬ ማነው መከታ አንባዬ ማነው ማነው (3x) እግዚአብሔር ነው በልዑል መጠጊያ አንባ መሽጐ ሚኖር ሁሉንም በሚችል አምላክ ጥላ ያድራል ከቶ አይሸበርም ከአዳኞች ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ከክፉ ከልሎ ይታደገው የለ ሕያው እግዚአብሔር የቀኑ ፍላጻ የሌሊቱ ግርማ አደጋና ጋኔል ተጓዥ በጨለማ ሺ በሺ ሲያረግፈው ሲያስረግጠኝ ኖርኩኝ እኔም ከእርሱ በታች መቀጥቀጥ ተማርኩኝ አዝ፦ አሁንስ ተስፋዬ ማነው (ጌታ ነው) ድጋፍ ምሶሶዬ ማነው (ጌታ) አለኝታ ጋሻዬ ማነው (ጌታ ነው) መከታ አንባዬ ማነው (ጌታ ጌታ ጌታ) ማነው (3x) እግዚአብሔር ነው ማነው (3x) እግዚአብሔር ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection