አቀበት ሜዳ ገደላ ገደል የታለፈበት የሚረሳ አይደል ነዳፊው እባብ ነካሹ አውሬ ስንት አስረገጠኝ በዚህ በእግሬ የሠማይ አምላክ አቤት ምህረቱ ማድረግ ይችላል ደካማን ብርቱ በእርሱ ሆናችሁ ያያችሁ ብዙ በዕልልታ ሆታ ምሥጋናን አብዙ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ መካሪ ወንድም ወላጅ አባቴ የሆነልኝ ሁሉ በሁሉ ቆርቁሮኝ አያውቅ ጠባይ አመሉ ጣቱን በመያዝ ዳዴ ተምሬ ቆሜ ለመሄድ ሆኖልኝ ዛሬ የጥንቱ አምላክ የልጅነቴ ዛሬም ላክብረው በአንደበቴ ይሄ ክፉ ዓለም ምኑ ይመቻል በሥጋ በደም የትኛው ሲቻል በየማለዳው አዲስ በሆነው በምህረቱ ነው ያልጠፋነው እንደ እኔ ቢሆን እንደድካሜ ዛሬም በፊቱ ባልታየሁ ቆሜ በዐይኔ እያየሁት አለፈ ስንቱ የያዘኝ አምላክ እግዚአብሔር ብርቱ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ መካሪ ወንድም ወላጅ አባቴ የሆነልኝ ሁሉ በሁሉ ቆርቁሮኝ አያውቅ ጠባይ አመሉ ጣቱን በመያዝ ዳዴ ተምሬ ቆሜ ለመሄድ ሆኖልኝ ዛሬ የጥንቱ አምላክ የልጅነቴ ዛሬም ላክብረው በአንደበቴ ይህን ዮርዳኖስን ስሻገረው ደረቅ በትር ነው በእጄ የነበረው ዛሬ ግን ይሄው ዓለመለኝ በተዐምራቱ እያስገረመኝ ሕይወት ዥንጉርጉር ቀለሙ ብዙ መች ቀላል ሆነ ጓዙ መዘዙ የሰበሰበኝ የያዘኝ ጌታ ስሙ ከፍ ይበል በዕልልታ ሆታ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ መካሪ ወንድም ወላጅ አባቴ የሆነልኝ ሁሉ በሁሉ ቆርቁሮኝ አያውቅ ጠባይ አመሉ ጣቱን በመያዝ ዳዴ ተምሬ ቆሜ ለመሄድ ሆኖልኝ ዛሬ የጥንቱ አምላክ የልጅነቴ ዛሬም ላክብረው በአንደበቴ