እስከዛሬ የጠበቀኝ በእጁ ይዞ ያለቀቀኝ የክርስትናን ቀጭን መንገድ የሕይወትን ውጣ ውረድ ባይበዛልኝ የእርሱ ፀጋ አንዷም ሌሊት አትነጋ ዛሬም ቆምኩኝ በዚህ ቦታ ስሙ ይክበር የእኔ ጌታ (2x) አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና እንደጠላት አሳብ ቢሆን ከሆነልኝ አንዱም አይሆን ታሪክ ቢያብብ ሕይወት ቢያምር ሁሉም ነገር በእርሱ ተዐምር ከእያንዳንዷ እስትንፋስ ስጦታ ናት የኢየሱስ ከፈቀደ ይሁን ካለ አይሆንም የሚል ማን አለ (2x) አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና አንተ . (1) . ቀናተኛ መቼም ቢሆን አትተኛ እንደተራበ አንበሳ ዙሪያዬን ብትዞር እያገሳህ ልትውጠኝ ብትመኘኝ ሲያምርህ ይቅር አታገኘኝ በስሙ አጥር በደሙ እሳት ከልሎኛል የእኔ አባት (2x) አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና ያንን ዘንዶ እባቡን የወጋኸው ወገቡን ራስ እራሱን ያስረገጥከኝ ስንቱን ነገር ያስመለጥከኝ ኢየሱስ የእኔ ጋሻዬ በክፉ ቀን መሸሺያዬ መቆሚያዬ ነህ አለቴ ላመስግንህ በአንደበቴ (2x) አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ አላለቀምና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምህረትህ ቸርነትህ ከቶ አያልቅምና