Song Lyrics

ድረስልኝ

Pastor Tamrat Haile
Bedibibikosh Kenu Endayalf
በጉድለት ነው የምመላለሰው የሞላሁኝ እመስላለሁ ለሰው ያውቀው የለ ጌታ ውስጤን ዘልቆ ግብዝነት የትም አይሄድ ርቆ አዝ፦ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ቀባብቼ ውጬዬን አሳምሬ ማስመሰሉን እንጃ ከየት ተምሬ መቅረብ ትቼ ሆኜ እራሴን አዘገየው መጐብኘት ፈውሴን አዝ፦ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ አውቀዋለሁ ባሕረ ገሊላ አይካድም አሳም እንደሞላ የማጥመድስ ልምድ መች አጥቼ ልሂድ እንጂ ዋናውን ረስቼ አዝ፦ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ ለረድኤት እጄን አነሳለሁ ኧረ ወዴት ወዴት ሊኬድ ከቶ የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ አንተን ትቶ አዝ፦ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ይህ አየነ ስውር ደግመህ ብትዳስሰው አጥርቶ አየ ለይቶ ዛፍ ከሰው ደግመህ ዳሰኝ እኔንም ጌታዬ እልፍ ይበል ይስፋ እይታዬ አዝ፦ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅልን እባክህ ጠጥተንህ እንድንባረክ ለልጆችህ ላለን በበረሃ ፍሰስልን አንተ የሕይወት ውሃ አዝ፦ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ ድረስልኝ (4x) ምርኮዬን መልስልኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection