Song Lyrics

አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው

አዝ፦ አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም አንተን ጠብቆ ባዶ የቀረ መከራ ገጥሞት የተማረረ አላየሁኝም አልሰማሁኝም ያለፈው ዘመን ታሪክ ይመርመር ከቶ አይገኝም አዝ፦ አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም ሥጋ ለባሹን የተደገፈ በሰው ስራ ላይ አይኑ ያረፈ ምርኩዙ ሲወድቅ እሱም ወደቀ አንተን ያለው ግን የማታ ማታ ደስ ብሎት ሳቀ አዝ፦ አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም እኔም ባለፈው ሰውን አይቼ ተጎድቻለሁ መንገዴን ስቼ ከእንግዲህ አንተን እጠብቃለሁ ዛሬ ባለቅስም የማታ ማታ እኔም ስቃለሁ አዝ፦ አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም የእምባዬ ፍሬ ለምልሞ ባላይ ቢያጠወልገው የበጋው ፀሀይ የመጨረሻው ዝናብ ይዘንባል የእኔም ፈተና ከነኮተቱ ገደል ይገባል አዝ፦ አንተን መጠበቅ ብዙ ትርፍ አለው ለታገሰ ሰው ፀጋህ ላስቻለው አንተን ጠብቆ ያፈረ የለም በዚህ ምድር ይሁን በወዲያኛው አለም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection