Song Lyrics

ትሻለኛለህ አባባ

አዝ፦ ኑሮዬ ከአንተ ጋራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ የደስታ ቢሆን የዕንባ ትሻለኛለህ አባባ ሊያጠግብ ኩርማን እንጀራ ቀንና ሌሊት ብሰራ አለቀ ኃይሌ ጉልበቴ በክንድህ ጥቂት ዘመኔ በአንተ ቤት ልረፍ መድህኔ (2x) አዝ፦ ኑሮዬ ከአንተ ጋራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ የደስታ ቢሆን የዕንባ ትሻለኛለህ አባባ ከዛሬ ነገ ይሻል ብዬ ብዙ ሮጥኩኝ ጨርቄን ጥዬ በዓለም ያየሁት አበሳ እስከመቼም አይረሳ ከእንግዲህ በቃ ሩጫዬ መስቀልህ ሆኗል ምርጫዬ (2x) አዝ፦ ኑሮዬ ከአንተ ጋራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ የደስታ ቢሆን የዕንባ ትሻለኛለህ አባባ ክፉ ዓለም ክብር የጐደላት ጦር እንጂ ሰላም የሌላት ሰው በአምላክ አምሳል ተፈጥሮ ወደ አውሬነት ተቀይሮ እርስ በርስ ስታብላላ በውሸት ዕውቀት አታላ (2x) አዝ፦ ኑሮዬ ከአንተ ጋራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ የደስታ ቢሆን የዕንባ ትሻለኛለህ አባባ የዚህ ዓለም ጌታ ከመሆን ሰማይን ምድርን ከመግዛት እራስን ላንተ አስገዝቶ ድሃ ተብሎ መጠራት ክብር እንደሆነ አወቅሁ ጠንቅቄ (2x) በቤትህ ልኑር ማቅቄ አዝ፦ ኑሮዬ ከአንተ ጋራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ የደስታ ቢሆን የዕንባ ትሻለኛለህ አባባ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection