Song Lyrics

ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ያያሉ

አዝ፦ ጌታ ምስኪኖችን ይወዳል ጐስቋሎችን ይወዳል ሰው የጣለውን ያነሳል የተረሳውን ያስታውሳል ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ያያሉ ለዓይነስውራን መሪ ነው ለአካለ ስንኩል ድጋፍ ነው ለረሃብተኞች መጋቢ ወላጅ አልባውን ሰብሳቢ ለደሃ አደጐች አባት ነው ለመበለቶች ዳኛ ነው ሃዘንተኛውን ያጽናናል ጌታ ለሁሉም ይሆናል ጌታ ሰርግ ቤት ይገኛል ውሃውን ወይን ጠጅ ያደርጋል በለቅሶም በሀዘን ቦታ ተገኝቶ ያጽናናል ጌታ ህመመተኛውን ደጋፊ አስታማሚ አልጋ አንጣፊ ሐኪም ነው በሽታን ያውቃል ፈዋሽ ነው ነጻ ያወጣል ካህን ነው ሕዝብን ይመራል ንጉሥ ነው ያስተዳድራል ወታደር ነው አገር ጠባቂ ከአውሬ ከአንበሳ ነጣቂ አገር ሲወረር በግፍ ሕዝብ እንደ ቅጠል ሲርግፍ ከምስኪኖች ጐን ይቆማል መርከቡን በባሕር ያሰጥማል ሃዘን ትጥቅህን አይፍታ ችግርክን ንገር ለጌታ አያልፍም ከንፈሩን መጥጦ ያነሳል እጅን ጨብጦ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection