Song Lyrics

ሶስት መንገድ የለም

Pastor Tamrat Haile
Ahunim Alew Bemerkebu
ያዝ ለቀቅ ሔድ መጣ ገባ ወጣ ሕይወት ትርጉም ሲያጣ ወይ ከየሱስ ወይ ከዓለም ምረጥ እንጂ ሦስት መንገድ የለም እንጀራ ለመብላት ሺ ተሰበሰበ መስቀል ለመሸከም አንድም አልቀረበ ተዓምር ለማየት እልፍ ሰው ቢንጋጋ ኢየሱስ ብቻ ነውበጦር የተወጋ :አዝ፦ ያዝ ለቀቅ በየመንገድ ወራጅ ሞልቷል ተሳፋሪ ከጠጣ በኋላ ወጭቱን ሰባሪ ትላንትን አትርሳ አትሁን ውለታ ቢስ ገባ ወጣ አትበል ጸንተህ ቁም በየሱስ :አዝ፦ ያዝ ለቀቅ ድንኳን አስከሚወርድ ድግስ ተጠናቆ ስደት አስኪመጣ ነጻው ዘመን አልቆ ስንት ሰው ዘምሯል ስንቱስ አጨብጭቧል በመከራው ቀን ግን ጌታ ብዙዎችን ታዝቧል :አዝ፦ ያዝ ለቀቅ እራሱን ላይገዛ ላይችል መታዘዙን በሞቅታ ጊዜ ቃል ኪዳነ ብዙ ሆኖለት ላይከፋል ስለት የተሳለ አሁን በዚህ መሃል ባለዳ ስንት አለ? :አዝ፦ ያዝ ለቀቅ መና ካዘነበ ከምንጩ ካጠጣን ከአመድ አንስቶን ከረግረግ ካወጣን ካበላን ካጠጣን ካከበረን ኋላ መስቀሉን አንሽሽ አብረን እንጉላላ :አዝ፦ ያዝ ለቀቅ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection