አዝ፦ ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ ከወህኒ ከፍርድ እኔኑ ሊያወጣ ከድንግል ማርያም ሥጋ ለብሶ መጣ መልክ ውበቱን ተወ የባርያን መልክ ያዘ እስከ መስቀል ሞት በፍቅር ታዘዘ ከአደረገው በቀር ኢየሱሴ ምንም ታሪክ የለኝ የእራሴ አዝ፦ ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው በመስቀሉ ግርግር በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ በቃሉ እውነተኛ በተግባሩም ደግ ከፋት የሌለበት የእግዚአብሔር በግ እኔን ሊያዘምረኝ እርሱ አለቀሰ እኔን ሊያከብረኝ ወረትን ለበሰ ከሥም ሁሉ በላይ ሥም አለው ዛሬም ምሥጋናዬ ለእርሱ ነው አዝ፦ ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው በመስቀሉ ግርግር በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ ብዙ የነበረውን እዳዬን ሻረልኝ ኃጢአቴን ሁሉ ከኋላው ጣለልኝ በመስቀል ጠርጐ ከእኔ አስወግዶ ጨካኙን ከሳሼን ባዶ እጁን ሰደደው እዛጋ ጀመረ ታሪኬ ምሥጋና ይብሳለት አምላኬ አዝ፦ ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው በመስቀሉ ግርግር በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (2x)