አዝ፦ ክብር ክብር ክብር ጌታ ለአንተ ይሁን በሰማይ በምድር መካኒቱን በልጅ የባረካት ደስ የተሰኘች ሴት ያደረካት ምስኪኑን ከአመድ ያነሳኸው ለሹመት ሽልማት ያበቃኸው :አዝ፦ ክብር ክብር ክብር ባሕሩን ለሁለት የከፈልከው ሾላውን ከስሩ የነቀልከው ለደካማው ኃይልን የሰጠኸው በከፍታዎች ላይ ያራመድከው :አዝ፦ ክብር ክብር ክብር ዘንዶውን የወጋህ የቆራረጥክ ጠንካራውን አለት የሰነጠክ የተራበችውን ነፍስ ያጠገብክ የተበተኑትን የሰበስብክ ክብር ለአንተ ይሁን :አዝ፦ ክብር ክብር ክብር የእስረኞችን ጩኸት አዳምጠሃል የወህኒውን መዝጊያ ሰባብረሃል ሰው የረሳቸውን አስታውሰሃል ያልጋ ቁራኞችን ፈውሰሃል ክብር ለአንተ ይሁን :አዝ፦ ክብር ክብር ክብር