አዝ፦ ሠላም ኢየሱስ ነው ፍቅር ኢየሱስ ነው እረፍት ኢየሱስ ነው ደስታ ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው (3x) ለነገድ ለጐሳ ሠላም ኢየሱስ ነው በአገሮች መሃል ሠላም ኢየሱስ ነው ለሰባቱ አህጉራት ሠላም ኢየሱስ ነው ለዓለም በሙሉ ሠላም ኢየሱስ ነው ከሰው ምን ይገኛል ሥጋ ከለበሰ ባንዱ ስናማርር ይመጣል የባሰ ይኸኛው ሲያጠራ ያኛው ሲያደፈርስ ባለንበት መሔድ ውኃ ቅዳ መልስ አንዴ ከጠጣን እንዳንጠማ የችግር ወሬ እንዳንሰማ ማረፍ ከፈለግን እስክወዲያኛው ጌታ ኢየሱስ ነው የሰላም ዳኛው አዝ፦ ሠላም ኢየሱስ ነው ፍቅር ኢየሱስ ነው እረፍት ኢየሱስ ነው ደስታ ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው (3x) በቤተስብ መሃልሠላም ኢየሱስ ነው ለባለትድሮች ሠላም ኢየሱስ ነው ለወንድም ለሴትም ሠላም ኢየሱስ ነው ለያንዳንዱ ሕይወት ሠላም ኢየሱስ ነው ሠይጣን ጥላውን ሲጥል ገብቶ ሲያምታታ ቤተሰብ ሲበትን ትዳርን ሲፈታ ቤቶች ፈረሱና ተዘጉና ደጆች ጐዳናውን ሞሉት የመንገድ ዳር ልጆች ምስቅልቅል ላለ ሕብረተሰብ ሩቅ አያስኬድም መፍትሔው ቅርብ የጌታን መንግሥት ጽድቁን ብትሹ አሁን ይፈታል ዕንቆቅልሹ አዝ፦ ሠላም ኢየሱስ ነው ፍቅር ኢየሱስ ነው እረፍት ኢየሱስ ነው ደስታ ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው (3x) ማታ ስንተኛ ሠላም ኢየሱስ ነው ጥዋት ስንነሣ ሠላም ኢየሱስ ነው በመንገድ ስንሔድ ሠላም ኢየሱስ ነው በሥራ በዕረፍት ሠላም ኢየሱስ ነው እስቲ ዕራስህን ባትደልል ምን አለ ጢርነቱ እንደሆን በልብህ ውስጥ አለ ሲጋራ ብታጨስ ጫትም ብትበላ ውስኪ ብትጠጣ አረቂና ጠላ መተንፈሻ ነው አፍንጫ አይደል ጭስ ማውጫ ሳንባ ሲቃጠል አንጀት ሲንጫጫ አበላሽቶታል ወዝብ ጠረንህ የሚያሳምር ኢየሱስ አለልህ አዝ፦ ሠላም ኢየሱስ ነው ፍቅር ኢየሱስ ነው እረፍት ኢየሱስ ነው ደስታ ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው (3x)